top of page
Search

Paving the path to a brighter future

Updated: Apr 28, 2020

የድርጅቱ ዋና ዋና አላማዎች፣ 1, ወላይታ ህዝብ ኢትዮጵያ በሚባል ሀገር በአንዱ ክፍል የሚኖር መሆኑ አየታወቀ አንዳንድ ፅንፌኞች ወላይታን ልዩ ህዝብ አድርገው  ከአጎራባች ዞንኖችና ከመላ ኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በእኩልነት እንዳይኖር ለፓለትካ ጥቅም ሲሉ የምያደርጉትን እንቅስቃሴ ህዝቡ ተረድቶ ባህሉ የሆነውን አብሮነትና የሀገር ፍቅር ስሜቱን ጠብቆ እንድ ቀጥል ማስተማር፣ 2, በኢትዩጵያ የሁሉም ማህበረሰብ ቋንቋ ፣ ሀይማኖት፣ ባህና ማህበራዊ እሴቶች እንዲከበሩ መስራት፣ 3, የወላይታ ህዝብ በላዩ ላይ የተጫነውን የመብትና የነፃነት እጦት  በጋራና በአንድነት ቆሞ እንዲታገል ማበረታታት የህዝቡ ሉአላዊ መብትና ፍትህ እንዳይዛባ ጠብቃ ሆኖ መከራከርና ለሰብአዊ መብት ጥበቃ ከምሰሩ ከማንኛውም ድርጅት ጋር በጋራ መንቀሳቀስ፣ 4, ሌብነትን፣ ዘረኝነትን፣ ስንፍና፣ ዉሸትና ቅጥፈትን እንዲሁም ጎጠኝነትን፣ ጥላቻን፣ ፍራቻና ራስ ወዳድነት  ለእድገት ፀር የሆኑ አስተሳሰቦች በመላ እትዮጵያና በወላይታም እያደጉ መምጣታቸው አሳሳቢ ስለሆነ ይህ እንዲስፋፋ እድል የሚሰጠውን ሥርአትንም ጭምር ህዝቡ እንድታገል ማነሳሳት፣ 5, በመላ ኢትዮጵያ በሊዝ ስም እየተካሄደ ያለው የመሬት ወረራ በተለይ በወላይታ በርካታ አርሶ አደሮችን ያፈናቀለና የኑሮ ዋስትና ያሳጣ ከመሆኑም በላይ ጮሌዎች በአጭሩ እንድከበሩ እያደረገ ያለ በተለይ አርሶ አደሩ የመንግስት ጭሰኛ እንዲሆን ያደረገ በመሆኑ ይህ እንዲቆም ከሚታገሉ ክልሎች ጋር ተባብሮ መስራት፣ 6,  በማንኛውም ቦታና አካባቢ ሰው ስው መሆኑን በመቀበል ለሁሉም የሰው ዘር መብት እኩል መቆም ናቸው።


 
 
 

1 Comment


Dawit Alambo
Dawit Alambo
Apr 29, 2020

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽንን በተመለከተ ከአለም አቀፍ ኢትዮጵያዊያን ወላይታዎች ህብረት(አኢወህ) የተሰጠ ማሳሰቢያ፣

         ኮረና ቫይረስ በቻይና ከተከሰተ ጀምሮ በፈጣን ሁኔታ በአለም ተስፋፍቶ በሺዎች የሚቆጠር ህይወት ቀጥፏል፣ ቫይረሱ ዘር፣ ሀይማኖት፣ ፆታን፣ ሀብታምና ድሀን፣ አዋቂም ሆነ ባለሥልጥንን የማይለይ ጅምላ ጨራሽ መቅሰፍት ነው።

       በዚህ በሽታ በመላው አለም የምገኙም ሆን በሀገር ቤት ያሉ በርካታ እትዮጵያዊያን ተጠቅተዋል በያሉበት ሀገር  ከቤት እንዳይወጡ ታዘው ሚልዮኖች  እንቅስቃሴአቸውን አቁመው ራሳቸውን እየተከላከሉ ቢገኙም እንደአጋጣሚ ይሆንና በበሽታው የሚያዙም አሉ ።

     ይህን ማሳሰቢያ ለማስተላለፍ የተገደድንበት በተለይ በተወለድንበት ወላይታ ዞን ወረርሽኑን ለመከላከል ህዝቡ ትኩረት አለመሰጠቱን በየቀኑ በምናደርገው ክትትል በመረዳታችን ህዝባችን ይበልጥ እንዲጠነቀቅ በውጭ ያለን ያየነውን ለመመስከር አስበን ነው በዚህ በሽታ ተይዞ የሞተ ግለሰብ  ሰው እንዳይጠጋ ተደርጎ በዶዘር ጉድጓድ ተቆፍሮ 14 ሰው በአንድ  ቦታ ይቀበራል፣ ምስት ባሏን…

Like
Post: Blog2_Post

4039094988

Subscribe Form

Thanks for submitting!

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn

©2020 by Global Ethiopian Wolaita Union. Proudly created with Wix.com

bottom of page